ዜና

News

“ሰዓሊ የማነ ልዑል – በቴአትር 70 ዓመታት የምናስታውሰው

October 13, 2025  |  admin 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመታት መዳረሻ ላይ ኾነን ማንን እናስታውስ?
ሠዐሊ የማነ ልዑል ….‹‹ከዴጊያ›› ጋር
ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ/ም
ቴአትር ቤትን ከሌላው ተቋማት ለየት የሚያደርገው ዋናው ጉዳይ የኪነጥበብ ቤት መሆኑ ነው፡፡የሚነገርለት የሚመሰከርለት፤ የሚፃፍለት ባለ ተሰጥኦዎች እና የፈጠራ ሥራቸው ማዕከል መሆኑ፡፡ ጥቂት የማይባሉ የኪነጥበብ ሰዎች ደግሞ ሥራቸው ይጮሃል እንጂ እነሱ ስለራሳቸው ንግግርም ፣ዝናም የሚፈልጉም አይመስሉም፡፡ በቃ ዝም ናቸው፡፡ዝም ብሎ ሥራውን ሲሠራ ዐይናችን እሱ ላይ አረፈ ፡፡ ሠዐሊ የማነ ልዑል ላይ፡፡
ሸራውን ወጥሮ ፣ብሩሹን ወድሮ ሥራው ላይ ተመስጧል፡፡ ከሥራው ማናጠብ ቢከብድም ተዳፈርነው፡፡ ‹‹እንደምን ዋልክ የማነ ?›› አልነው ከተመስጦው ተመድርፎ ምላሽ ሰጠን፡፡ ከፊቱ ሰፊ ሸራ ተንጣሏል ፡፡‹‹ ምን እየሠራህ ነው?›› አልነው እየፈራን እየተባን ማራኪ ጅምር ሥዕሉ ላይ ዐይናችንን እያሯሯጥን፡፡‹‹ የዴጊያ›› ትውፊታዊ ቴአትር መልከዓ ምድር የመድረክ ገጹን እየሠራሁ…›› አለን፡፡
የ‹‹ዴጊያ›› ትውፊታዊ ቴአትር ደራሲ በጽሁፉ ውስጥ ያቀበለውን የምናብ ዓለሙን ሽራው ላይ ዕውን አድርጎታል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የምዕራብ ኦሞ ዞን መልክዓ ምድር ሸራው ላይ ፍንትው ብሏል፡፡ አጋጣሚውን አግኝተን እኛ ሄደን በዐይናችን ያየነውን ውብ ተፈጥሮ እርሱ በምናቡ ቀድሞን በብሩሹ እየሸመነው ነው፡፡ይገርማል የጥበብ ሰው አርቆና አሻግሮ የምናብ ዕይታ !የአስተውሎት ልህቀት!
ሠዐሊ የማነ ልዑል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለ 36 ዓመት አገልግሏል፡፡ በርካታ የሥዕል ሥራዎችን አበርክቶልናል፡፡ከነዚህም ውስጥ
የለሊት ርግቦች
የሠርጉ ዋዜማ
ካሊ ጉላ
የፍቅር ማዕበል
ከትዳር በላይ
የቃቂ ውርድወት
ባቢሎን በሳሎን
ንጉሥ አርማህ
12ቱ እንግዶች
ሠዐሊ የማነ ልዑል በፎቶው ላይ አንደሚታየው በብሩሹ ዕውን እያደረገ ያለው‹‹ ዴጊያ››ን ጨምሮ ከ 50 በላይ ሥዕልና ፖስተር እንዲሁም የህትመት ዲዘይንን ሠርቷል፡፡ሠዐሊ የማነ ልዑል በጡረታ እረፍት ላይ ቢሆንም በሞያው በተፈለገ ጊዜ እንዲህ በቴአትር ቤቱ እየተገኘ ብሩሹን ከሸራው እያዋሀደ አበርክቶውን አላቋረጠም፡፡
እናመሰግናለን!
Scroll to Top