ዜና
News
የሰልጣኞች ምልመላ በመካሄድ ላይ ነው
October 15, 2025 | admin
ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም
ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በ100 ቀናት ዕቅዱ መሠረት በሙዚቃና በቴአትር ዘርፍ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞችን በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች በመገኘት ምልመላ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ለዚሁ የምልመላ ታላቅ ሥራ የቴአትር ቤቱ መልማይ የኪነጥበብ ባለሞያዎች በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተሰማሩ ሲሆን የምልማላ ሥራው ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ምልመላው በየክልሉና በየከተማ መስተዳድሮች በሙዚቃና በቴአትር ዘርፍ በመካከለኛ ደረጃ በመሥራት ላይ ያሉትን ሞያተኞች ያለመ ሲሆን ከምልመላው በኋላ የሚሰጠው ስልጠና የሰልጣኞችን አቅም በማጎልበት ወደየመጡበት ክልል ተመልሰው ሌሎች የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማሰልጠን በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በማጋራት አቅም ለመገንባት የሚያስችል ትጥቅ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
በተያያዥ ከምልመላ በኋላ የሚሰጠው ስልጠና በተለይም በተወዛዋዥና በድምፃውያን በኩል በቴአትር ቤቱ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት በዚሁ ስልጠና የሚገኙ ባለ ልዩ ችሎታና ተሰጥኦዎች ቴአትር ቤቱን እንደሚቀላቀሉ መገለጹ ይታወሳል፡፡የሰልጣኞች ምልመላ በየክልሉና በየከተማ መስተዳድሩ በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል፡፡