ዜና
News
የዛሬው ስብሰባ ግን እንባም ነበረበት
October 16, 2025 | admin
ጥቂት የማንባል የሚያቃጥል እንፋሎት ተነፈስን፤ተቃጠልን፤ነደድን!!!
ጥቅምት 6 ቀን 2018
ብዙዎቻችን ስብሰባ ሲባል ወደ ሱቅ ሄደን፣ ማስቲካ ገዝተን ፣ በሻይ ሰዓት ሻይ ቡና ብለን ፣ይኽን ሁሉ አድርገን ከማዛጋትና ከማፋሸግ አያግደንም፡፡ ከጥቁር መነጽር ኋላ ጦሽ ብለን ተኝተን የምናኮራፋም አንጠፋም፡፡ ዛሬ ግን ለየት ይላል፡፡ ተቃጠልን!
በቀረበልን ሰነድ ውስጥ አሻግረን ኢትዮጵያ ላይ ከእንባ ጤዛ ጋር ትኩር አልንባት፡፡ይህች ሀገር! ይህች እናት ምድር በቀረበልን ሰነድ ውስጥ በቁጭት ቁልጭ ብላ ተስላለች፡፡ስትገፋ የኖረች ፤ከመገፋት ያላዳንናት ፤ በመገፋቷ ምክንያት የቆዳ ስፋትዋን ያጠበበች እና ዛሬ ያለችበት ደረጃ የደረሰች፤ያኔ ትላልቅ መርከቦች ለንግድ እና ለተለያዩ ሥራዎች የሚርመሰመሱባት ታላቅ እና ሰፊ ሀገር፤ ከአክሱም ስርወ መንግሥት እስከ መካከለኛው ዘመን ድረስ ኢትዮጵያ የጅኦስትራቴጂካዊ ቁመና ከልዕለ ሃያላን ሃገራት ተርታ ተሰልፋ በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበረች ሀገር ዛሬ መብቷን ያለ አግባብ ተገፍፋ መብቷን ለማሰከበር የምትዋትት እናት ምድር፡፡ ይቆጫል!
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ክቡር ነብዩ ባዬ ለሚኒስቴሩ እና የብሔራዊ ቴአትር ሠራተኞችን ጨምሮ ለተጠሪ ተቋማቱ ሠራተኞች የብሔራዊ ጥቅም እና ጂኦስትራቴጂካል ሰነድን አቀረቡልን፡፡የባህር በር ጥያቄ እውነተኛ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ሰነዱን ተንተርሰው ሲያቀርቡ ከብሔራዊ ጥቅም ጋር አያይዘው ነበር፡፡
የኢኮኖሚ ብልጽገና ፤በዓለም አደባባይ ተጽእኖ ፈጣሪነትን፣የባህል እና እምነት መከበርን፣ታሪክን፣ማሕበራዊ ዋስትናን ማስከበር፣በዓለም አደባባይ ሊኖር የሚችል ክብር ከባህር በር ጋር ያለውን ቁርኝት ክቡር ሚኒሰትሩ ፍንትው አድርገው አሳይተውናል ፡፡
ይኽች በዘመናት ውስጥ የወደብ ባለቤት የነበረች ታላቅ ሀገር ያልሰከነ የ ፓለቲካ ትርምስ ውስጥ በነበረ አሻጥር ምክንያት ወደብ አልባ መኾኗ የመላው ሕዝብ የእግር እሳት ሆኖ ለዓመታት ቆይቷል፡፡
ስለሰፊዋ ኢትዮጵያ ፤ስለባህር በሯ እና ታላላቅ ሀገራዊ አጀንዳዎችና የጋራ ብሔራዊ ጥቅሞች ከማሰብና ከመሥራት ይልቅ ባዳ እና ባንዳ በብሔርና በጎጥ እንድንሰነጣጠርና እንድንቆራቆስ አድረገውን አስተሳሰባችንን ጠፍንገው አስረውና አኮስምነው በብሔርና በጎጥ ላይ ተቸንክረን የኔ ዛፍ፣የኔ ተራራ ፣የኔ ድንበር፣የኔ ብሔር፣የኔ ጎጥ … እያልን ትልቁን ነገር አስጥለው እንደህፃን ልጅ በማያጣላው እንድንጣላ ብቻ ሳይሆን ወንድም ከወንድሙ እንዲጋደል ኾኖ ኖሯል፡፡
አሁንም ከዚህ የአስተሳሰብ ኩስመና ሙሉ ለሙሉ አልተላቀቅንም፡፡ታላቅ ሀገርን ከመሥራት ይልቅ ስለአንዲት ጠባብና ጊዜያዊ የስልጣን ወንበር በራስ ዜጋና ትውልድ ላይ ትምሕርት ቤት ጥርቅም አድረገን ዘግተን፣የህክምና ማዕከላትን አውድመንና ፣ መሠረተ ልማት አፍረሰን፣… በሀሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ጠመንጃ ታቅፈንና ወድረን በአስተሳሰብ ቀንጭረናል፡፡ ያሳዝናል!
ኢትዮጵያ ግን ታላቅ ሀገር ነች፡፡በ’ሷ ልክ ትልቅና ሰፊ አዕመሮ ሊገነባ እና እያንዳንዱ ሰው በአስተሳሰቡ ከፍታ ያለጠመንጃ ሊመጥናት ይገባል፡፡የትኛውም የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረን እንኳ የጋራ በሆነው ብሔራዊ ጥቅም ላይ እንደብረት ልንጠነክር የአድዋ ድል ታሪካችን የሚያስተቃቅፈን ዘላለማዊ እርሾአችን ነው!
የአድዋ ድል ልጆች ማሰብ ያለብን ስለሰፊዋ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የባህር በር ባለቤትነቷ ዳግም እንዲረጋገጥ እያንዳንዱ ዜጋ ኢትዮጵያ ጥንት በነበራት የስፋትና የስልጣኔ ልክ አዕምሮውን አስፍቶና አዘምኖ ለባህር በር ባለቤትነት ኃላፊነቱን በመወጣት ለብሔራዊ ጥቅሙ በጽናት በመቆም ከሉዓላዊነት ወደ ጆኦስትራቴጂያዊ የበላይነት ለመድረስ የበኩሉን ሚና በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት በጽናት እንዲወጣ ተቀንብቦ የቀረበው ሰነድ በብዙዎች ልብ ውስጥ የተዳፈነውን የቁጭት እሳት አጭሯል፡፡የሀገር ፍቅርን ቀስቅሷል፡፡
ታላቋ ኢትዮጵያ እንኳንስ አካሏ የነበረውን ቀይ ባሕርን በሕንድ ውቅያኖስ ዘይላ እና በርበራን ለረዥም ጊዜ ያስተዳደረች ታላቅ ሀገር የባሕር በር ፈተና የገጠማት ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን በቅኝ ግዛት ተቀራምተው ለማስተዳደር ወረራ ካደረጉ በኋላ እንደሆነ የዘርፉ አጥኚዎች ይናገራሉ ።በዚህ ሂደት በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች በአውሮፓውያኑ መዳፍ ስር ሲገቡ፤ ኢትዮጵያ ግን በጀግኖች ልጆችዋ ያልተበገረች ጠንካራ ሀገር በመሆኗ በቅኝ ግዛት መቆጣጠር ሲያቅታቸው ኾን ተብሎ ለመጉዳት በተጠቀሙት አማራጭም በዓባይ ወንዝ እንዳትጠቀም፤ከቀይ ባሕር ዳርቻም ርቃ ታዛቢና የበዪ ተመልካች እንድትሆን፤ መልካቸውን እንደእስስት በሚቀያይሩ አሻጥሮች ከባሕር በር ተሸቀንጥራ እንድትርቅ፤ ሀቋን እንድታጣ በግፍ ተደርጋለች፡፡
በተሸረበው ሴራ እና አሻጥር እንደ ግብጽ ያሉ የአረብ ሀገራት በዓባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያን ያላካተተ ኢፍትሐዊ ስምምነት ለማድረግ አጋጣሚውንም ያገኙት በዚህ ሰበብ ነው፡፡ ከዛሬ 34 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን ምጽዋን የምትጋራ ሀገር እንደነበረችና በምጽዋና አሰብ ወደቦች የገቢና ወጪ ንግዷን ታሳልጥ እንደነበር ከቶም አይረሳም ።
ከደርግ መንግሥት መገርሰስ በኋላ ሥልጣን የተቆጣጠረው ሕወሓት ለኤርትራ መገንጠል እውቅና በመስጠት ኢትዮጵያ ራሷ ገንብታ ስትጠቀምባቸው የነበሩ የአሰብና ምጽዋ ወደቦችን አሳጥቷታል ፤ጉዳዩ ስለኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ መፃኢ ጊዜ ምንም ሳያገናዝብ ኾን ተብሎ በገዛ ሀገር ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት አመራሮቿ መልካም ፈቃድ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑ አሳዘኝ እና ግራ የሚያጋባ እንቆቅልሽ ነው ሲሉ ብዙዎች በቁጭት ይገልጻሉ።
ኤርትራ በ1983 ዓ.ም በጦር ኃይል ትዕዛዝ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ የኢትዮጵያ ወደውጭ መተላለፊያና መግቢያ የባህር በር መዘጋትን ያህል ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣና ያሳዘነ ብሔራዊ ጉዳይና ጉዳት በሀገሪቱ ተከስቶ አያውቅም ፤ቀና ብሎ መጠየቅም እንደወንጀለኛ ስለሚያስቆጥር አንገታቸውን እንደደፉ ጥያቄውን ሳያነሱ እነሆ 34 ዓመት አለፈ፡፡ልጅ ተወልዶ የ 34 ዓመት ጎረምሳ ሳይሆን ጎልማሳ ሆነ፡፡
የታሪካዊ ጠላቶቻችን ያልተገራ ዘመን ተሻጋሪ ፍላጎት፣ በየዘመኑ ያሉ የሀገራቸውን ጥቅምና ክብር አሳልፈው የሚሸጡ ባንዳዎች በየዘመኑ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪዎች መሆን፣ የኢትዮጵያ ጂኦ ስትራቴጅያዊ ተፈላጊነት የፈጠረው ጫና፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ አለመጠናቀቅ፣ ድህነት፣ኋላ ቀርነት እና ሌሎችም የብሔራዊ ጥቅማችን ዋነኛ ፈተናዎች እንደሆኑ በክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ተዳስሷል፡፡
ይኽን በመረዳት የጂኦስራቴጂካዊ ቁመናዋ ወደ ተሻለ ቁመና አሸጋግሮ ሃገራችን የእድገቷን ማማ ከፍ አድርጎ በማስፈንጠር ብልጽግናዋን አውጃ በራሷ ቁመና ልክ ቀና ብላ በክብሯ ልክ እንድትቆም የባሕር በር ባለቤት እንደትሆን የጋራ ሀሳብ መያዝ የሀገር ወዳዶች ሁሉ የልብ ትርታ እና ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡
የባህር በር ለዚህች ታላቅና ጥንታዊት የኢትዮጵያ ሀቋ ነው፡፡ችሮታና ልግስና አይደለም! ሆኖም ብሔራዊ ጥቅሟን በተለያዩ ምክንያቶች ሳታስጠብቅ በመቆየቷ ከ30 ዓመት በላይ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ ኖራለች፡፡ ይበቃል!!! ሀቋን በሰላማዊ መንገድ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የምትጠይቅበት ታሪካዊ ጊዜዋ አሁን ነው፡፡ኹሉም በአንድነትና ከታላቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ከዚህ ታላቅ ሀሳብ ጎን ሊቆም ይገባል፡፡
ዛሬ በክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የቀረበው ሰነድ ይኽን ሁሉ የዳሰሰና ሰፊዋን ኢትዮጵያ በአመክንዮ እንድናስብ ያደረገ ነበር፡፡ዐይናችን እንባ ያጤዘው፤የተዳፈነ የቁጭት እንፋሎት የተነፈስነው ለዚህ ነው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትርና መላው የኪነ ጥበብ ሰው በዘመናት ውስጥ በሀገር ክብር የማይደራደር፤ ለሀገሩ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ሕይወቱን፣ ተሰጥኦውንና ክህሎቱን የሰጠ ነው፡፡እነጥላሁን ገሰሰ እያነቡ የዘፈኑላት ለዚህ ነው ፤የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ የእንባ ጣዕም ውስጥ ያለው የሀገር ፍቅር ነው፡፡እነ ብዙነሽ በቀለ እነ ሂሩት በቀለ እና ሌሎች ስለሀገር ሲያዜሙ አብረን የምንሰጥመው፤ ሀገር ከፍ የምትልብን የሀገርን ጥልቅ ፍቅር፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም በማስቀደም ሀቋን በዜማ ስለሚነግሩ ነው፡፡ስለዚህ ዛሬም ከኪነጥበቡ ማሕበረሰብ ከዚህ ቅኝት አንፃር አንድ በሚያደርገን በጋራ ብሔራዊ ጥቅም ላይ በሀገር ፍቅር ላይ የተመሰረተ ብዙ የኪነጥበብ ሥራ ይጠበቃል፡፡የባህር በር ኖሮን ያላየ የባህር በር ብዙም የማያሳስበው ትውልድ በ30 ዓመታት ውስጥም እንዳፈራን በኪነጥበቡ ልብ ማለትና አስተሳሰብ ላይ መሥራት አለበት ባይ ነን፡፡