ዜና

News

ቅንጡ እና ዘመናዊ ቴአትር ቤት በአዲስ አበባ

October 11, 2025  |  admin 

ቅንጡ ፣ ዘመናዊና አስደሳች ቴአትርቤት በመዲናችን!
ጉብኝት ተካሄደ ፡-
የአዲስ አበባ ከተማ የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ሁለገብ የቴአትር ማዕከል /Art complex/ን የኪነጥበብ ቤተሰቦች እንዲጎበኙ ለኢትዮጵያ በሔራዊ ቴአትር በድርጀቱ በቀረበው ጥሪ መሠረት መስከረም 30 ቀን 2018ዓ/ም በኪነጥበብ ባለሞያዎችና በጄነራል ካውንስል አባላት ተጎብኝቷል፡፡
ይኽ ዘመናዊ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ሀገርን እና ሕዝብን ባከበረ ደረጃ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ ዘመናዊ ቴአትር ቤት ነው፡፡
ይኽ ቴአትር ቤት ሀገር ተረካቢ በኪነጥበብ የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተተኪ ትውልድን አዝናንቶ ለማነጽ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጎብኚዎች በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ባረከ ታደሰ በጉብኝቱ ላይ በሰጡት አስተያየት ቴአትር ቤት ተጠናቆ ለዚህ እንዲበቃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ እና በየደረጃው አስተዋጽኦ ያደረጉትን አመስግነዋል፡፡
ቴአትር ቤቱ ባለ14 ወለል ህንፃ
2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶች
የቲያትር አዳራሽ
3 የተለያዩ አዳራሾች
ሆቴል እና ሪስቶራንት
ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችና የፓርኪንግ አገልግሎት ያለው ነው፡፡
Scroll to Top