ዜና
News
ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው – በብሔራዊ ቴአትር 70 ዓመታት የምናስታውሰው
October 10, 2025 | admin
በ70 ዓመታቱ ውስጥ ማንን እናስተውስ?
ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን ይዞ እነሆ ህዳር መጣ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ እነማን ነበሩ? ብለን ስናስብ በሥራቸው አብሪ ኮከብ ሆነው ያለፉ በርካታ የኪነጥበብ ሰዎች ከነ ሙሉ ክብራቸው ትውስ ይሉናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ብዙም ያልተነገረለት ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው ግዘፍ ነስቶ በሥራዎቹ ዛሬም ሕያው ሆኖ ይደምቅብናል፡፡
ሰዓሊ ደምሴ ሽፈራው ከእናቱ ከወ/ሮ ገበያነሽ ዘርፋና ከአባቱ ከደጃዝማች ሺፈራው እርገጤ ጥር 10 ቀን 1943ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር ደሴ ከተማ ልዩ ስሙ ዳውዳ በተባለ ስፍራ ተወለደ::
የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በደሴ እቴጌ መነን አንደኛ ደረጃና በወ/ሮ ስህን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል:: ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የህይወቱ ጥሪ የሆነውን የስዕል ትምህርት ለመማር ከአዲስ አበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ገብቶ በ1969 ዓ.ም በቀለም ቅብ ዘርፍ በዲፕሎማ ተመርቋል::
ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው ትምህርቱን በጨረሰበት በዚሁ በአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ከነሐሴ 23 ቀን 1969ዓ.ም እስከ ነሐሴ 1 ቀን 1971 ዓ.ም ድረስ በመምህርነት ካገለገለ በኃላ ወደቀድሞው ሶቪየት ህብረት በመጓዝ በዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭ የሥነ ጥበብ ኢንስቲትዩት በጀመረው የስዕል ሙያ በቀለም ቅብ ዘርፍ የማስትሬት ዲግሪውን አግኝቷል::
የሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ እናት ሀገሩ ተመልሶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመቀጠር ከመስከረም 26 ቀን 1979 ዓ.ም ህይወቱ እስካለፈችበት ግንቦት 2 ቀን 1995 ዓ.ም ድረስ በመድረክ ገፅ ዲዛይነርነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አገልግሏል::
ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሥራ ከጀመረበት አንስቶ ለ16 ዓመታት ከ8 ወሮች በጠንካራ የሥራ ፍቅርና በፍፁም የሙያ ብቃት ጥበባዊና ሀገራዊ ግዴታውን ያለአንዳች መታከት ሲወጣ የኖረ ድንቅ ሰዓሊ ነበር::
ከ1979 ዓ.ም እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የቀረቡ ቴአትሮችን፣ የልዩ ትዕይንተ ጥበባት ዝግጅቶች፣ የሙዚቃ ትርዒቶችና ሙዚቃዊ ድራማዎች በሙሉ በ ደምሴ ሺፈራው የመድረክ ዲዛይንና የመድረክ ገጽ ስዕሎች የታጀቡና የተዋቡ ናቸው::
ሰዓሊ ደምሴ ሺፈራው እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለሞያው የታመነ፣ በአካልም ሆነ በመንፈስ ከቴአትር ቤቱ ተነጥሎ ውሎ ማደር የማይሆንለት፣ ለመድረክ ልዩ ፍቅርና ከበሬታ ያለው ፣በቀን ከ12 ሰዓት በላይ ሠርቶ ደከመኝን የማያውቅ፤ ራሱንና ህይወቱን ለሙያው አሳልፎ የሰጠ እውነተኛ የጥበብ ሰው ነበር::
ደምሴ ሺፈራው የአንዲት ሴት ልጅ እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር::
ይህ ድንቅ ሰዓሊ ድንቅ የመድረክ ገጽ ስዕሎቹንና የፖስተር ሥራዎቹን ትቶልን በተወለደ በ52 ዓመቱ ግንቦት 2 ቀን 1995ዓ.ም 4:30 ላይ በሞት ተለይቶናል:: ዘመን ነጎደ ፤እርሱም አረፈ፡፡ መደረክ ገጽ ስዕሎቹ ግን አሁኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚንተገተጉ ሕያዋን ሆነው አሉ፡፡