ዜና
News
ዲፕሎማቶች፣ የጥበብ ባለሙያዎች እና ልዩ እንግዶች
March 6, 2026 | admin
ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች ቀረቡ፡፡
የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ‹‹70 ዓመታት በ70 ቀን››በሚል መርሃ-ግብር በማጠቃለያ ዝግጅቱ መሠረት ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የተለያዩ ዝግጅቶች ቀረቡ፡፡
በዕለቱ የፎቶና የአልባሳት ዓውደ ርዕይ የጎበኙ ሲሆን ፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ታሪክን እና የአዲሱ ቴአትር ቤት ግንባታን በተመለከተ ለዲፐሎማቶቹና ለተገኙት እንግዶች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር አቶ ባረከ ታደሰ ለዲፕሎማቶቹና ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ቴአትር ቤቱ ዋናዋና ሥራዎችን በማስተዋወቅ ከሀገራት ጋር ኪነጥበብ ስላለው ትስስር ገልጸው እንግዶቹ ስለመገኘታቸው አመስግነዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ወክለው የተገኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጀነራል አምባሳደር ነብዩ ተድላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ለዲፕሎማቶቹና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኪነ ጥበብ ባህልን እና ሀገርን ለማስተዋወቅ ፤በሀገራት መካል ትስስር ለመፍጠር አንዱ መንገድ እንደሆነ በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡
በዕለቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ታላቁ የቫረይቲ ኦኬስትራ ቡድን ለዲፕሎማቶቹና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የሙዚቃ ዝግጅቶችን አቅርቧል ፡፡