ዜና
News
አርቲስት አሰለፈች በቀለ – የኪነጥበብ ጀግናችን እረፍት አገኘች
March 21, 2026 | admin
በኪነጥበብ ዘርፍ ጀግናችንን አጥተናል።
ዜና እረፍት
በኪነጥበቡ ዘርፍ ጀግናችንን እጥተናታል።
መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም
ከልጅነቷ ጀምሮ ተስጥኦዋን ሳትሰስት ከነሙሉ ክብሩ ለኪነጥበቡ ዘርፍ የስጠችው አን ጋፋዋን አርቲስት አሰለፈች በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች።
ትወዳጅዋ አርቲስት አስለፈች በቀለ ከልጅነቷ ጀምሮ በጡረታ እረፍት እስከተገለለችበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር በባህል ሙዚቃና በቴአትር ዘርፍ ደከመኝ ፣ሰለቸኝ ሳትል ያገለገለች ታላቅ አርቲስት ስትሆን በኢትዮጽያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ደማቅ አሻራዋን እሳርፋለች።
ይህች ታላቅ የኪነጥበብ ስው በመላው ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ውጭ ሀገራት በመዞር በባህልና ኪነጥበብ ዘርፍ የሀገርዋን ገጽታ የገነባች ፣ሀገርዋን ለዓለም ያስተዋወቀች የዘርፉ ጀግና ነበረች።
እርቲስት አሰለፈች በቀለ በሀገረ አሜሪካ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈች ሲሆን በመጪው ሳምንት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤተስቦችዋ፣የሥራ ባልደረቦችዋ ፣አድናቂዎችዋ በተገኙበት የእስከሬን ሽኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለቤተስቦችዋ፣ ለባልደረቦችዋ፣ለወዳጅ ዘመዶችዋ ፣ለመላው ሕዝብ መጽናናት ይሁን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር