ዜና
News
ድጋፍና ክትትል ተካሄደ
October 31, 2025 | admin
ጥቅምት 21 ቀን 2018
አዲስ አበባ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የማኔጅመንት አካላት ጋር በ2018 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ዕቅድና አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
በመግቢያው ላይ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዓሊይ ከማሎ የቡድን ዓላማ በመግለጽ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ በየነ ጎንፋ በዕቅድ መሠረት በተከናወኑ ሥራዎችን ለቡድኑ ያቀረቡ ሲሆን የቴአትርና የሙዚቃ እንዲሁም ና ሌሎች የየዘርፉ የሥራ መሪዎች አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ለይ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ የዕቅድ አፈጻጸሙ ያለበት ደረጃ በሰነድ ምልከታ ጭምር የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ሊሠሩ የሚገባቸው ተግባራት ላይ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል፡፡ እንደአጠቃላይ ካለፈው በጀት ዓመት በተሻለ ተቋሙ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የገለፀ ሲሆን ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል፤ የታዩ ድክመቶች ላይ ጠንክሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡