ዜና
News
ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተመሠረተበት 70ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ እንደቀጠለ ነው
November 24, 2025 | admin
ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመት የምሥረታ ከብረ በዓል ከኅዳር 3 ቀን 2018 ዓ/ም በደማቅ የመክፈቻ ሥን-ስርዓት መከፈቱ ይታወሳል፡፡ 70ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ተከትሎ ከኅዳር 13 ቀን 2018 እስከ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ/ም ቴአሮች እና ዓውደ ርዕይ ማቅረብ የቀጠለ ሲሆን በዚህም መሠረት ቅዳሜ “እምዬ ብረቷ ” እና “የሕይወት ታሪክ” ፤ እሁድ “ንጉሥ አርማህ” እና ” 12 እንግዶች” ቴአሮች ቀርበዋል፡፡ በርካታ ታዳሚያን ቴአትሮችን የተመለከቱ፤ ዓውደ ርዕዩን የጎበኙ ሲሆን ከቅዳሜ እስከ ቅዳሜ የቴአትርና የሚዚቃ እንዲሁም የዓውደ ርዕይ ዝግጅቶች የቴአት ቤቱን 70ኛ ዓመት በማስመልከት ለታዳሚያን በነፃ ማቅረብ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
የቴአትር ቤቱን 70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለታዳሚያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ብሐራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር እጩ ዶ/ር ባረከ ታደሰ በመልዕከታቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሎሪት ፀጋዬ ገመድኅንን፣ ረ/ፕ ተስፋዬ ገሠሠ ን፤የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠን እና ሌሎች ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች ያፈራና የመሩት ታላቅና በላግርማ ሞገስ ተቋም መሆኑን አስታውሰው ግርማውና ማስፈራቱ የመጣው ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች ሙሉ ጊዜና እውቀታቸውን ሰጥተው ያዘጋጁበት፣የፃፉበት፣ የመከሩበት፣የተወኑበት ያዜሙበት በመሆኑ ነው፡፡ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም አሁን ላይ 70 ዓመቱን ሲያከብር በታሪኩ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ12 ክልሎች እና ከ2 ከተማ መስተዳድሮች የተወጣጡ ወደ 400 የሚጠጉ እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ባለተሰጥኦችን ለማሰልጠን ሰልጣኞች ከየክልሉ የተመለመሉ ሲሆን ከስልጠናው በኋላ ከእነዚህ ውስጥ 50 ባለልዩ ተሰጥኦ ዕንቁዎች ብሔራዊ ቴአትር ይቀላቀላሉ ብለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ታሪካዊ ቅርስነቱን ሳይለቅ መታደስ አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ወንበሮቹ 70 ዓመትን አብረው ያከበሩ ሲሆኑ ታሪካዊነታቸውን ሳይላቁ ሊታደሱ ይገባል፡፡ ለአጠቃላይ እድሳቱ ኢነኒጂነሮች፣ባለሀብቶች አርቲስቶች ትብብር እንዲያደርጉና በታረክ ውስጥ በወርቅ ብዕር የሚጻፍ ደማቅ አሻራቸውን አንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡