ዜና
News
በሪፖርት አዘገጃጀት ፣ በኦዲት የአሠራር ሥርአት ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጠ
December 07, 2025 | admin
አዳማ
ኀዳር 28 ቀን 2018 ዓ/ም
በሪፖርት አዘገጃጀት ፣ በኦዲት የአሠራር ሥርዓት ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሥራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ ። ስለጠናው በቴአትር ቤቱ ስተራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ የተዘጋጀ ሲሆን በስልጠናው መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር እጩ ዶ/ር ባረከ ታደሰ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው ዕቅድ ዝግጅትን ለመፈተሽ፣ ሁሉም በዕቅዱ መሠረት ተናቦ ለመሥራት ፣ የላቀ ሥራ ለማፍለቅ እንደሚረዳ የገለፁ ሲሆን ኦዲትን በተመለከተ ተቋሙ የተሰጠውን ዓላማ ከግብ ለማድረስና ክፍተቶችን ለማስተካከል የሚረዳ በመሆኑ ከስልጠናው ግብአት መውሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ኦዲት ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ያለው፣ ሥራዎች በሕግና በመመሪያ እንዲሠራ የሚያግዝ፤ የሚያስተምር መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ለቴአትር ቤቱ ለሚያደርጉት ቀና ትብብር እንዲሁም አሰልጣኞችን አመስግነዋል።
ስልጠናው ከኅዳር 27ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት በኢፌዴሪ ባሕልና ስፖርት የዘርፋ ባለሞያ አቶ ጌታሁን ገዛኸኝ እና ወ/ሮ አይናለም ከበደ ሲሆኑ የዕቅድ ምንነት ፅንሰ ሀሳብና ባሕሪያት፣ዕቅድ ከክትትልና ግምገማ ጋር ያለው ተያያዥነት እንዲሁም የሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
በተያያዥ በገንዘብ ሚኒስቴር የህጋዊነትና ክንዋኔ ኦዲት ዲቪዥን ኃላፊ ወ/ሮ ዓይናለም ከበደ ኦዲትን በተመለከተ በሰጡት ስልጠና የ ኦዲት ምንነት እና ጥቅም ፣ስልጣንና ኃላፊነት፣እንዲሁም አስተዋፅኦው ላይ ትኩረት በማድረግ የተብራራ ሲሆን በስልጣኞች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በአሰልጣኞቹ ምላሽ ተስጥቷል።