ዜና

News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የባህል ቡድን የፀረ ሙስናን ቀን ክብረበዓል ላይ የባህል ሙዚቃዎች አቀረበ

December 10, 2025  |  admin 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የባህል ቡድን የፀረ ሙስናን ቀን ክብረበዓል ላይ የባህል ሙዚቃዎች አቀረበ፡፡
ኅዳር 30፣ 2018 ዓ.ም
የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር “ትውልድን በሥነ ምግባር፣ ተቋምን በአሠራር” በሚል መሪ ቃል በተከበረ የፀረ-ሙስና ቀን የታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የባህል ቡድን የሙዚቃ ሥራዎቹን እዲሁም የሙስናና በሙስና ላይ የሚደረግ እልህ አስጨራሽን ትግልን የሚያሳይ ሥነ-ግጥም ቀርቧል፡፡
በዕለቱ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትና ንብረት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል፤ ሌብነትን ለመከላከል የአሠራር ሥርአቶችን ማዘመን እንደሚያስፈልግ የባሕልና ሰፖርት ሚኒስቴር ሚኒሰትር ክብርት ሸዊት ሻንካ የገለጹ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ የሙስናን ምንነት፣ አስከፊነትና መፍተሔው የሚያስረዳ መነሻ ኦዲዮ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በመጨረሻም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ሰነድ ለፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማስረከብ መድረኩ ተጠናቋል።
Scroll to Top