ዜና

News

በሥራ አፈፃፀም ምዘናና እና በፌዴራል ሠራተኞች እዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

January 25, 2026  |  admin 

በሥራ አፈፃፀም ምዘናና እና በፌዴራል ሠራተኞች እዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። በ2018 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፓርት ቀረበ።
ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም
አዳማ
ለኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር ለየዘርፉ ሥራ አሥፈፃሚዎች አና ቡድን መሪዎች አዲስ በሚተገበርው የሥራ አፈፃፀም ምዘና አና በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353 /2017 እና አዋጁን በማስፈፀም በወጣው ምልመላና መረጣ አፈፃፀም መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጠ።
ስልጠናውን የሰጡት በሲቩል ሰርቪስ ኮሙሽን የሥራ አመራር ዴስክ አቶ ሳዱዲን ተማም ሙሱ እና የሰው ሀብት ሕግ ስምሪት ባለሞያ አቶ አየለ ደምሴ ናቸው።
በስልጠናው ስለእፈፃፀም ምዘና ዓላማና አተገባበር ሠራተኞች ሊከተሏቸው በሚገባ የሥራ ባህል ፣መፍትሄ አፍላቂነት፣ግብረገብነት፣ ግልፅንት፣ እውነተኛነት የመሳሰሉት ዕሴቶች ከሥራ ውጤትና ከሥራ አፈፃፀም ጋር ያላቸው መስተጋብር ተዳሷል።
በዕለቱ የ 2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሪፖርት በስትራቴጂክና ዕቅድ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ በየነ ጎንፉ የቀረበ ሲሆን የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር ክቡር አቶ ባረከ ታደስ በቀጣይ ሊተገበሩ በሚገባቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ስጥተዋል።
Scroll to Top