ዜና

News

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል

March 1, 2026  |  admin 

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል የአደባባይ ትርዒት በማቅረብ በድምቀት ተከበረ።
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ/ም
እዲስ አበባ
130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር ከባቢ አደባባይ ላይ ታሪካዊ ይዘት ባላቸው ሙዚቃዎች እና ሙዚቃዊ ቴአትር ለታዳሚያን በማቅረብ በድምቀት ተከበረ።
ዝግጅቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዕዝራ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ሲሆን “ዳግማዊ ዓደዋ” የተሰኘ ታሪካዊ ተውኔት፣ ልዩ ልዩ ሀገራዊና ታሪካዊ ጥዑመ ዜማዎች በአደባባይ በማቅረብ በዓሉ በድምቀት ተዘክሯል።
በዕለቱ ለተገኙት ለዓድዋ ድል ዝክረ በዓል ታዳሚያን ንግግር ያደረጉት የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር አቶ ባረከ ታደስ የዓድዋ ድል የመላው ሕዝብ የነፃነት ቀንዲል መሆኑን እስታውስው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቴአትር ቤቱ የዓድዋን ድል በአደባይ ሲያከብር የመጀመሪያው መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ አባቶቻችን በጎሳ ፣ በብሔር ፣በኃይማኖት ሳይለያዩ ታሪክ ሠርተው ቀዳማዊ ድል ስጥተውናል ያሉ ሲሆን ዛሬ ላይ ሕያው የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለዚህ ትውልድ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ሲለ ገልፀዋል።
የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሕዝብ እይቀሬ ሳልሳዊ ድል መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር የድል ስኬቱን ለማርጋገጥ በኪነጥበቡ ዘርፍ መትጋትና በጋራ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
Scroll to Top