ዜና

News

ድጋፍ እና ክትትል ፅንሰ-ሀሳብ ዙሪያ ለሥራ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

November 11, 2025  |  admin 

ኅዳር 2 ቀን 2018
አዲስ አበባ
ተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈፃሚ የተዘጋጀ በድጋፍ እና ክትትል ፅንሰ- ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለሥራ አመራሮች ተሰጠ፡፡ ስልጠናው በክትትልና ግምገማ ፅንሰ ሐሳብ እና ሂደት ፣የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ግንባታና ዘላቂነት የተለያዩ አካላት ሚና ላይ ያተኮረ ሲሆን
የክትትልና የግምገማ ዕቅድን ከአፈጻጸም ጋር በማነጻጸር ያለው ክፍተት የሚፈተሽበትና የሚጠበቁ ውጤቶች መገኘታቸው የሚረጋገጥበት ሥርዓት መሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫውን ባቀረቡት በአቶ ደሳለኝ አያሌው ተብራርቷል፡፡
በተያያዥ ድጋፍና ክትትል ተቋማቱ በዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ ለማወቅና የተሻለ አፈፃፀም ለመፍጠር ከፍ ያለ ሚና እንዳለው የተገለጸ ሲሆን በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር አቶ ባረከ ታደሰ ቴአትርና ሙዚቃ የተቋሙ ቁልፍ ሥራ እንደሆነ ገልፀው በባህል ላይ የሚሠሩ ሥራዎች ላይ ክትትል ማድረግ፤የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱ እና ያልተፈቱ ተብለው ተለይተው ሊታወቁና በዕቅድ ሊሠራባቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Scroll to Top