ዜና

News

የፎቶና የአልባሳት ዓውደ ርዕይ ቀረበ

March 14, 2026  |  admin 

መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ “የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል 17ኛው አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ከመጋቢት 05 እስከ 07/2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በድምቀት የተከፈተ ሲሆን በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የኃይማኖት አባቶች፣አበገዳዎች፣ሀደስንቄዎች፣አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችና ከአሥራ አንዱም ክ/ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በፌስቲቫሉ የተለያዩዩ የኪነ-ጥበብ ውድድሮች፣ ዐውደ ርዕዮች እና ልዩ ልዩ ሥነ-ጥበባዊ ክዋኔዎች፣ በዕይታዊ፣ በክውን እና በሥነ-ፅሑፋዊ ጥበባት ዘርፎች የተዘጋጁ አዝናኝ እና አስተማሪ ሥራዎች በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ቀርበዋል።
መርሃ ግብሩ ላይ በከተማዋ የሚገኙ የሥነ-ጥበብ ተቋማት፣ ቴአትር ቤቶች፣ የአ.አ.ዩ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤቶች፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የሙያ ማህበራት በአንድ መድረክ ያስባስበ ነው።
​በዚህ ታላቅ ፌስቲቫል ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር “የጥበብ ስጦታ ለሀገር ከፍታ” በሚለው የፌስቲቫሉ መሪ ቃል መሠረት ሀገራቸውን በኪነጥበቡ ዘርፍ ከፍ ያደረጉ፣በሥራቸው የሀገር አንድነትን እና ሉዓላዊነትን ያስከበሩ፣እያዝናኑ ያስተማሩ ጉምቱ የኪነጥበብ ሰዎችንሥራዎችን የሚይሳይ የፎቶ እና የአልባሳት አውደ ርዕይ ያቀረበ ሲሆን ዓውደ ርዕዩ በአዲስ አበባ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ኃላፊ ክብርት ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ፣በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና በበርካታ ታዳሚዎች የተጎበኘ ሲሆን በ ጉብኝቱ ላይ ለታደሙ ተማሪዎች እና ለኪነጥበበብ ማህበራት ስለ ታላላቅ ሥራዎቻቸው ገለፃ ተደርጓል።
ፌስቲቫሉ እስከ መጋቢት 7ቀን 2018 ዓ/ም የሚቀጥል ሲሆን ዓውደ ርዕዩም በእነዚህ ቀናት ቀጣይ ሆኖ ለታዳሚያን ይቀርባል።
Scroll to Top