የካቲት 6ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሠራተኞች ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2018 ዓ/ም በተለያየ ምክንያት ኮሚቴ ሆነው ሊሠሩ በማይችሉ የዲሰፕሊን ኮሚቴ ምትክ አራት የኮሚቴ አባላት ምርጫ አካሂደዋል፡፡የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ለሠራተኞቹ የዲሰፕሊን ኮሚቴውን ማሟላት አስፈላጊነትን በመገልጽ ምርጫውን የመሩት የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር እጩ ዶ/ር ባረከ ታደሰ ሲሆኑ ኮሚቴ ሆነው ሲሰሩ በመመሪያና በደንብ ሕግን በአግባቡ በመተርጎም መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በተያያዥ የመስክ ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በጉብኝቱ አዲሱ ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት ግንባታ እንደገና መጀመሩ በዋና ዳይሬክተሩ የተገለፀ ሲሆን ሠራተኞቹ የአዲሱን ቴአትር ቤት ግንባታ ሂደት ላይ ምልከታ አድርገዋል፡፡