ዜና
News
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመት ‹‹70 ዓመት በ 70 ቀናት›› በሚል መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
Feburary 26, 2026 | admin
የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመት ‹‹70 ዓመታት በ 70 ቀናት›› በሚል መርሃ ግብር የተለያዩ ዝግጅቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በመርሃ ግብሩ መሠረት የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ/ም የማርች ባንድ የተለያዩ ሀገራዊ ጥዑመ ዜማዎችን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መግቢያ ላይ እና ዝግጅቱን ሰፖንሰር ባደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዘመናዊ (ስተሪንግ) የሙዚቃ ቡድን በንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ሥራዎችን ያቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሰንደቅ ዓለማ በክብር የመስቀል ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡
በዕለቱ የቡና ጠጡ ሥነ-ስርዓት.፣ የፎቶና የአልባሳት ዐውደ ርዕይ ጉብኝት ፤እንዲሁም ‹‹ንጉሥ አርማህ›› ቴአትር ለንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት እና ለሌሎች አጎራባች መሥሪያቤት ሠራተኞች ቅርቧል፡፡
ዐውደ ርዕዩን ያስጎበኙት እና በቴአትሩ መክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር ባረከ ታደሰ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን ሰፖንሰር ስላደረገ በማመስገን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ ታላቅ ሥራ እየሠራ መሆኑን በማስታወስ አመስግነው በቀጣይ በባሕልና በኪነጥበቡ ዘርፍ በጋራ እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል፡፡
በተያያዥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያቤትን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ ኃይለየሱስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በሀገር አንድነት፣ በታሪክ እና በሰው ልጅ ሕይወት ገጠመኝ ዙሪያ በርካታ የኪነጥብብ ሥራዎችን የሠራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ባንኩ ክፍያዎችን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይ እየተነጋገርን በጋራ እንሠራለን ብለዋል፡፡