ዜና

News

የሴቶች ድምጽ ለእኩልነት – “እምዬ ብረቷ” በማርች 8

March 14, 2026  |  admin 

ማርች 8/ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን/ ‹‹የሴቶች ደምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ››በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
‹‹እምዬ ብረቷ›› ቴአትር ለማርች 8 ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ለታዳሚያን ቀረበ፡፡
የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ/ም
በዓለም ለ 115 በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ለ 50ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን በማስመልከት ‹‹እምዬ ብረቷ›› ቴአትር ከተለያዩ ተቋማት ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች፤ እንዲሁም ለቴአትር ቤቱ ሠራተኞች ቀረበ፡፡
በዕለቱ ለታዳሚያኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር አቶ ባረከ ታደሰ ሴት የተከበረች ነች ፤መብቷ መከበር፤ ድምጽዋ መሰማት አለበት፡፡ሆኖም ከባሕላችን ያፈነገጠ ፌሚኒዝም የሚያቀነቅኑ አስተሳሰብ ሴት ልጆችን የሚበሉ እና የሚያጠፉ ልምምድ ላይ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ሲሉ አመላክተዋል፡፡
ሴቶች በኢኮኖሚ፣በፖለቲካ ፣በመሪነት ረገድ ወደፊት መምጣት አለባቸው፤ ይችላሉ፤ ያከናውናሉ፡፡ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በፓርላማ የሴቶች ውክልና 50 ፐርሰንት እንዲሆን እየተሠራ ነው፤ በመሪነትም በትልቅ ስኬት እየቀደሙ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረበት በአድዋ ጦርት ላይ ንግሥት ጣይቱ፤ሸዋሰገድ ገድሌን የመሳሰሉት በርካታ ጀግኖች እናቶች ለሀገራቸው ያበረከቱትን ተጋድሎ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡
በቤት ውስጥ ወንዶች ልጆች እናቶቻቸውን ማገዝ እንዳለባቸው ይኽም በየቤቱ መጎልበት እንዳለበት፤ወላጆች በዚህ ላይ መሥራት እንዳለባቸው ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰለማዊት ዞይብ በበኩላቸው ‹‹የሴቶች ደምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል ቀኑ እንደሚከበር አስታውሰው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 የመከበር ፋይዳን በተመለከተ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በታላቁ መራሒ ተውኔት ማንያዘዋል እንደሻው ተተርጉሞ የተዘጋጀው “እምዬ ብረቷ” የተሰኘው ታሪካዊ ቴአትር በዕለቱ ለታዳሚያን ቀርቧል፡፡
Scroll to Top