አርክውድ የመጀመሪያው የአፍሪካ የፊልም ገበያ እና የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትጽያ ብሔራዊ ቴአትር የፎቶ አውደ ርዕይ አቀርበ።
የፊልምና የሙዚቃ ከያንያንን ያገናኘው አርክውድ የመጀመሪያው የአፍሪካ የፊልም ገበያ እና የሽልማት ስነ ስርአት ስንጋ ተራ በሚገኝው የፊልም ኮምፕሌክስ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን የኢትዮጽያ ብሔራዊ እና የፊልም እንደስትሪው ባለሞያዎች በሥራዎቻቸው ዙሪያ አውደርዕይ አቅርበዋል።
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነጥበብ ስነጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) የፊልም ገበያ እና የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከዘርፉ ባለማያዎች ጋር የፎቶ አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።