ዜና
News
ምሽቱ ፀሀይ የሆነበት የምስጋና ቀን
November 10, 2025 | admin
ታላቁ ሁለገብ አርቲስት ጌትነት እንየው ብቻ ሳይሆን ኪነ-ጥበብ በታላቁ የኪነጥበብ ዋርካ ጥላ በሚገባት ልክ ከፍ ያለችበት ወርቃማና ደማቅ ምሽት!!
ታላቁ አርቲስት ጌትነት እንየው ቤተስቦቹ፣ የጥበብ አጋሮቹ ፣አድናቂዎቹ ጥሪ የትደረገላቸውእጅግ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት በላቀ አክብሮት ተመሰገነ! ተሸለመ!
ተወዳጁ አርቲስት ለመሽለም ሲል አልሠራም ።ግን 43 ዓመታትን በሞያ ትጋትና ፍቅር ኖረ። የአስተዋዮቹ የሕዝብ ልጆች ዐይኖች ደግሞ ትጋቱን፣ለሞያው ያለውን ፍቅርን አተኩረው ያዩ ነበሩ ። ስለሚገባው አርአያነቱን በታላቅ ክብር አይረሴ አና ታሪካዊ እድርገው በደማቅ ክብር ጭምር ለትውልድ ና ለታረክ አሻገሩት!! በታላላቅ ሥራው ምክንያት አከበሩት !
ዛሬ ኅዳር 1ቀን 2018 ቤተሰቦቹ፣ከያኒያን ጓዶቹ ታዳሚያን በተገኙበት 68ኛ የልደት በዓሉንና የ43 ዓመታት የሞያ አገልግሎቱን አበርክቶ በተመለከተ በስጦታ የታጀበ መርሐ ግብር በታላቁ የኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር ተከናውኗል።
ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ ባዘጋጀው እና በርካታ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት በዚህ እጅግ ደማቅና ልዩ መርሐ ግብር ላይም እንዲህ ተደረገ።
የባህልና ስፓርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብና ሥነጥቡብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ረ/ ፕ ነብዩ ባዬ በሁለገቡ አርቲስት ጌትነት እንየው ሕይወትና መልካም ሰብእና ዙሪያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ።
የሞያ አጋሩ አርቲስት ኃይሉ ፅጋዬ ለሁለ ገቡ አርቲስት ጌትነት እንየው የሎሪትነት ማዕረግ ሊስጠው እንደሚገባ ጠይቋል።