Views: 0

May be an image of 1 person, sitting and indoor
 
በዝግጅቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች ፣የኦሮሚያ ባህል ማዕከል በስልጠና ላይ
ያሉትን ሰልጣኝ ወታደሮች ስፍራው ድረስ በመሄድ እያበረታቱ መሆናቸውን አስታውሰው ሠላማችንን
ለማስከበር ሁሉም መዝመት አለበት ብለዋል።መዝመት በግንባር ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ
እንዲህ ከጀርባ ሆኖ ስንቅ ማቀበልም አንዱ የዘመቻው አካል ነው ፡፡እናቶቻችን ዘመቻን ከመምራት
ስንቅ እስከማቀበል ታላቅ ተግባር በአድዋ ጦርነት ላይ ፈፅመው አድዋን አሸንፈው የጥቁር ህዝቦችን
ነፃነት አረጋግጠዋል ።ጦርነቱ ከውስጥ ብቻ ሳይሆን የውጭም ስለሆነ የሃገራችንን ሠላም በማስጠበቅ
እኛ ሴቶች እንደ እናቶቻችን ዘብ በመቆም ዳግማዊ አደዋን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል፡፡
በእስካሁኑ እንቅስቃሴ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና እና ተጠሪ መስሪያ ቤቶች
ደምወዛቸውን ሰጥታዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች ለሠራዊቱ አስፋለጊ ስራዎች ደም መለገስን ጨምሮ
ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሚኒስትሯ ይህ እያዘጋጀነው ያለውን ስንቅ ግንባር ድረስ በመሄድ
ለጀግናው ሰራዊታችን እናቀብላለን ብለዋል፡፡ከምሳ ሠአት በኋላ በነበረው የዳቦ ቆሎ ስንቅ ዝግጅት
ላይ የተገኙት ብርጋዴል ጄኔራል አስረስ አያሌው በስንቅ ዝግጅቱ ላይ በአካል በመገኘት ባስተላለፉት
መልእክት አሸባሪውን የጁንታ ቡድን ለመደምሰስ የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ከጀመርን ጊዜ
አንስቶ ድሉ ስኬታማ እንዲሆን መላው ህብረተሰቡ ጫፍ አስከ ጫፍ በገንዘብ፣ በሠው ሀይል፣ በስንቅ ፣
በሎጂስቲክ፣ በደም ልገሳ በአጠቃለይ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ የሰራዊቱ ሞራል ከፍ እንዲል
ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል ብለዋል፡፡አሁን ባለው የህልውና ዘመቻ አሸባሪው ቡድን ከሌሎች
አሸባሪዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበታተን ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን
የገለጹት ብርጋዴል ጄኔራል አሥረስ አያሌው ይህንን ወረራ ለመቀልበስ መላው ህዝብ እየተንቀሳቀሰ ነው ፡፡
የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትም የሉአላዊት ሀገር ጉዳይ ነው፤ የህልውና ጉዳይ ነው፤
ብለው በገንዘብም በስንቅም ለሚያደርጉት ስራ የእንቅስቃሴው አንዱ አካል በመሆኑ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ባለፉት ወራት የትግራይ ህዝብ እፎይታ እንዲያገኝ አርሶአደሩ የእርሻ ስራውን በሰላምና
በመረጋጋት ውስጥ ሆኖ አንዲያከናውን እንዲሁም ለህዝቡ የሚደረገው ድጋፍ ያለፅጥታ ችግር ለህብረተሰቡ
እሰከቀበሌ ድረስ እንዲደርስ በመንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም የተደርገ ቢሆንም ይህንን ተኩስ አቁም
አሸባሪው ህዋሀት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም አጎራባች በሆኑ በአማራና በአፋር ክልሎች ከፍተኛ
ወረራና ትንኮሳ በመፈጸም ወደ 300ሺህ ሰው አፈናቅሏል፤ንብረት ሰርቆ ወደትግራይ አጓጉዟል፤ሴቶችን
እና እናቶችን ደፍሯል ፤ የህዝብና የመንግስት የልማት ተቋማት አውድሟል ብለዋል፡፡
ይህ አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብአተ መሬቱ እንዲፋጠን መላው ህዝብ ከፍተኛ
እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ፡፡እናንተም የዚህ ታሪክ አካል ናችሁ ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት
ብ/ጄኔራል አስረስ አያሌው እያንዳንዱ ግለሰብ፣ማሰህበረሰብ ባጠቃላይ ሀገራችን በመኖርና ባለመኖር
ትግል ላይ ይገኛሉ፡፡ይህአሸባሪ ቡድን ካልጠፋ ኢትዮጵያ ሀገራችን አትቀጥልም፤ ትበታታናለች፡፡
አሸባሪው ህዋሃት ከውጭ ካሉት ከቅርብም፣ ከሩቅም ጠላቶቻችን የውክልና ግዳጅ ተቀብሎ ከፍተኛ
ትርምስ እየፈጠረ ነው፡፡ ሀገራችን በተለያየ ጊዜ የተላያዩ ችግሮች አጋጥሟታል፡፡ግን አንድም ጊዜ
ተንበርክካ አትታውቅም፡፡ በብዙ ችግሮቻችን ውስጥ ባንዳዊ ተሳትፎ ነበር ግን ባንዳ አሸናፊ ሆኖ
አያውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ታሽነፋለች ብለዋል፡፡