ነሀሴ 03 ቀን 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ተስማሙ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዛሬ ባደረጉት የጋራ ውይይት ባላቸው አቅም ሁሉ የሐገር መከላከያ
ሰራዊትን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ችግሮች ሁሉ ሁልጊዜም
የሚጠበቅበት ኃላፊነትና ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በአሁኑ ጊዜም
ለተፈጠረው ሀገራዊ ችግር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ
መሆኑን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡የወር ደመወዝን መስጠት፣ በቴአትር ቤቱ ውስጥ የሙዚቃ
ኮንሰርት በማዘጋጀት እና ቴአትሮችን በማሳየት የሚገኘውን ገቢ ለሰራዊቱ ገቢ በማድረግ፣
በደም ልገሳ እና በሌሎችም የጉልበት ስራዎች ለመሳተፍ ሰራተኞቹ ቃል ገብተዋል፡፡
የቴአትር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ አስረስ እና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ውበቱ ወርቄ ሰራተኞችን ባወያዩበት ጊዜ እንዳሉት መከላከያን
መደገፍ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አወያዮቹ የተነሱትን ሀሳቦች በማጠቃለል የወር ደመወዙን መስጠት የሚችል
ደመወዙን በመስጠት፣ “ለገበታ ለሀገር” የወር ደመወዛቸውን የሰጡ እና በመክፈል ላይ ያሉ
ሰራተኞችን በተመለከተ ደግሞ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመወያየት መፍትሄ
እንደሚሰጠው፣ የሙዚቃና የቴአትር ስራዎችን በማቅረብ ገቢውን ለድጋፉ ማዋል የሚለው
ላይ ደግሞ ከዳይሬክቶሬቶቹ እና ከሚመለከታቸው ክፍል ጋር ውይይት በማድረግ በፍጥነት
ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
+3
 
 
2424