News/ዜና

በአዳማ ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

 


     የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለመላው የቴአትር ቤቱ አመራሮችና
ሰራተኞች ከመስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ሲሰጥ
የነበረውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አጠናቀቀ፡፡በሶስት ዙር በተሰጠው
ስልጠና ላይ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ማንያዘዋል እንደሻው የመክፈቻ
ንግግርና የማነቃቂያ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን አቶ ደስታ አስረስ
የቴአትር ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ለስልጠናው የማጠናቀቂያ መልዕክት
አስተላልፈዋል፡፡በለውጥ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በህዝብ ግንኙነት
እንዲሁም በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ያተኮሩ የግንዛቤ
ማስጨበጫ ርዕሶች በቴአትር ቤቱ አሰልጣኞች ቀርበው ሰፊ ውይይት
ከተደረገባቸው በኋላ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ስልጠናው
ቀጣይነት እንደሚኖረው አቶ ውበቱ ወርቄ የሰው ኃብትና ልማትና
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጠቁመዋል፡፡

 

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡

   

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ በዓል ቅዳሜ 
መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠን
የተመለከተ ዶክመንታሪ ፊልም እና የተለያዩ ሙዚቃዎች
በቴአትር ቤቱ እና ተጋባዥ አርቲስቶች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም በታዋቂ አርቲስቶችና የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች
ማህበር ፕሬዘዳንት መልዕክቶችም ተላልፈው ፕሮግራሙ
"ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ" በሚለው ህብረ-ዝማሬ ተጠናቋል፡፡