ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም በተከናወነው ፕሮግራም ላይ አቶ ወሰንየለህ መብረቁ የሙዚቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የዝግጅቱን ዋና ዓላማ ከገለጹ በኋላ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማንያዘዋል እንደሻው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
            በአዲስ ዓመት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለሙያዎች እና በተቋሙ አደረጃጀት ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላደረጉ አካላት ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የኢፌዴሪ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኢታ እና የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማንያዘዋል እንደሻው የምስጋና የምስክር ወረቀት ሽልማት አበርክተዋል፡፡
            በፕሮግራሙ ላይ መላው የቴአትር ቤቱ ሰራተኞች፣ የኢፌዴሪ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የተለያዩ የማህበራት ተወካዮች፣ በአዲስ ዓመት ዝግጅት ላይ የተሳተፉ አርቲስቶች፣ ከዩኒቨርስቲ የመጡ ባለሙያዎች፣ ስፖንሰሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡